ወያኔ አጥፍቶ ለመጥፋት የመጨረሻውን መሰናዶ እያደረገ መሆኑ ግልፅ ሆኗል
የትግሬ-ወያኔ ላለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ፣ በተለይም በዐማራው፣ በኦሮሞው፣ በሱማሌው፣ በሐዲያው፣ በአኙዋኩ፣ በኑዌሩ፣ በከፊቾው፣ ወዘተርፈ ላይ የፈጸመው የዘር ፍጅት፣ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ሊፈጸም ቀርቶ ለማሰብ አስቸጋሪ ነው። ግፉ ከገደቡ አልፎ በመትረፍረፉ፣ የዚህ የከፋ የዘር ፍጅት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ሰለባ የሆኑት ነገዶች ተወላጆች፣ በዳያቸው የሆነውን የትግሬ-ወያኔ በቃህ ካሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። ለዚህ ማረጋገጫውም፣ በየአካባቢው በባዶ እጃቸው እስከ አፍንጫው ከታጠቀው ገዳይ ኃይል ፊት በመቆም በተከታታይ የሚያሰሙት የተቃውሞ ድምፅና ሰላማዊ ሰልፍ በግልጽ ያሳያል።
የትግሬ-ወያኔ ትውልድ በምድጃ ዙሪያ ከአያት ቅድመ-አያቶቹ ተግቶት ያደገው የዐማራ ጥላቻ እጅግ የሠፋና ሥር የሰደደ መሆኑ ይታወቃል። ለዚህም ሥር የሰደደ ጥላቻ ዋና ማሳያው፣ ገና የትጥቅ ትግል ሲጀምር፣«የትግራይ ሕዝብ ደመኛ ጠላት ዐማራ ነው!»፣ «ወያኔ ዐማራን ሳያጠፋ አንዳችም እረፍት አይኖረውም!» የሚል »መሪ ሀሳብ» በፕሮግራሙ ነድፎ መንቀሳቀስ የጀመረ መሆኑ ነው። በዚህ ጥላቻ ላይም ተመሥርቶ፣ ዘረኛው አገዛዝ ባለፉት 25 ዓመታት ብቻ ከ5 ሚሊዮን በላይ ዐማሮችን ከምድረ-ገጽ አጥፍቷል። ሌሎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ዐማሮች ለዘመናት ከኖሩበት አካባቢ ሀብት ንብረታቸውን ነጥቆ በማባረር ለከፍተኛ ችግር ዳርጓቸዋል፤ በቁጥር ከአንድ ሚሊዮን ተኩል የማያንሱትን ዐማሮች ከኢትዮጵያ ምድር አሰድዷል። ይህ በዐማራ ጥላቻ ተወልዶ ያደገና ዐማራን ለማጥፋት የተደራጀ ዘረኛ ቡድን፣ ካለፈው ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ፍትኅ በጠየቁ የዐማራው ተወላጆች ላይ የዘር ፍጅት በመፈጸም ላይ መሆኑን የዓለም የመገናኛ ብዙኃን በሥፋት እየዘገቡት መሆኑ ይታወቃል።