Amharic

የዛሬ ሰኞ ጥቅምት ፯/፪ሺህ፱ ዓም የሞረሽ ዐማራ ሬድዮ ስርጭትን ያድምጡ

የዐማራ ድምጽን ለመርዳት ይህን ተጭነው ዐቅምዎ የፈቀደውን ይለግሱ ዘንድ በደል በሚደርስበት ወገናችሁ ስም በትሕትና እንጠይቃለን

https://www.gofundme.com/voice-of-amara-radio-support-fund-2tvf94s

 

ዐማራው ዛሬም እንዳትሞኝ ነቅተህ ጠብቅ!

Saturday, October 8, 2016

ምንም ጊዜው ቢረዝም፣ የመከራ ጊዜ አይረሳም። ያለፉት 25 ዓመታት የትግሬ ወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈጸመው ሁለንተናዊ በደል ምንጊዜም የሚረሳ አይደለም። እንርሳህ ብንለው ሊረሳ የሚቻል አይደለምና! ላለመረሳቱ ምክንያት የሚሆነውም እያንዳንዱ በደል በድምፅ፣ በምስል፣ በሰነድ ተመዝግቦ የተያዘ ከመሆኑም ባሻገር፣ የበደሎቹ ዓይነት በዓለም ላይ ያልታዩ ዘግናኝና ሰቅጣጭ በመሆናቸው፣ እንርሳው ብንል ከኅሊናችን ጓዳ ተሽጠው የሚረሱ አይሆኑም። «ሥራ ለሠሪው፣...Read more

በ9/19/2016 በዋሽንግተን ዲሲ ኢትዮጵያውያን ባደረጉት የተቃውሞ ሕዝባዊ ሰልፍ አቶ ተክሌ የሻው የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ሊቀመንበር ያደረጉት ንግግር፣

Saturday, October 1, 2016

 የተከበራችሁ እህት ወንድሞቼ የእናት ኢትዮጵያ ልጆች!  ለወገናችን ድምፅ ለመሆን ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የመጣችሁ ውድ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያዊያት! ይህ የዛሬው የተቃውሞ ሰልፍ፣ የትግሬ ነፃ አውጭ ድርጅትን ዘረኛ አገዛዝ በመቃወም ብቻ የሚገልጽ ሳይሆን፣ የወያኔ ቡድን በልኩ ቀልሶ ካስገባን የጎሣ ጎጆዎች መውጣታችንና ወያኔ የቀማንን ኢትዮጵያዊ ማንነታችንና አንድነታችን መልሰን የተጎናጸፍን መሆንችን ለዓለም ማኅበረሰብ ያሳየንበት ሕዝባዊ ሰልፍ ነው። ይህም...Read more

የዐማራው ነገድ የጅምላ ፍጅትና ተጋድሎ ማስረጃዎች በከፊል!

Saturday, September 10, 2016

ዐማራው ከ1972 እስከ 2008 ዓም ባሉት ዓመታት በዘረኛው የትግሬ ወያኔ በጠላትነት ተፈርጆ ከፍተኛ የሆነ የዘር ጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል የተፈጸመበት መሆኑን ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ባለፉት አራት ዓመታት ተከታታይ መግለጫዎችን ማውጣቱ ይታወሳል። በዚህም መሠረት በአጠቃላይ በወያኔ የዘር አገዛዝ ከ5 ሚሊዮን በላይ ዐማሮች ከምድረ-ገጽ እንዲጠፉ ተደርጓል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ፣ ከዐማራው የጸዱ አካባቢዎችን ለመፍጠርና ዐማራውን አሰቃይቶ፣ አደህይቶና ከሰው...Read more

ሞረሽ ለዐማራ ሕዝብ!!! ከሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የተሰጠ የነፍስ አድን ጥሪ!

Wednesday, August 31, 2016

የተከበርከውና ጀግናው የዐማራ ሕዝብ ሆይ!  
የትግሬ ወያኔ አገዛዝ «ዐማራውን አከርካሪውን ሰብረነዋል»፣ «ዐማራው ላይመለስ ገድለን ቀብረነዋል» በማለት ይሳለቅብሃል። በእርግጥም ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ከአምስት ሚሊዮን በላይ ዐማሮችን ገድሎ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ደግሞ አሰድዶ ከመኖሪያ ቀያቸው አፈናቅሏል። ሆኖም ግን ከሞቱት በላይ፣ ካሉት በታች ሆነህ የምትኖረው የቀረኸው ዐማራ፣ ከገባህበት የቁም መቃብር ለመውጣት ዘወትር ትግልህን እንዳላቋረጥክ...Read more

ዐማራው፣ አሁንም በዘረኛው የትግሬ ወያኔ አገዛዝ የዘር ፍጅት እየተፈጸመበት ነው!

Thursday, August 25, 2016

ወያኔ አጥፍቶ ለመጥፋት የመጨረሻውን መሰናዶ እያደረገ መሆኑ ግልፅ ሆኗል

የትግሬ-ወያኔ ላለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ፣ በተለይም በዐማራው፣ በኦሮሞው፣ በሱማሌው፣ በሐዲያው፣ በአኙዋኩ፣ በኑዌሩ፣ በከፊቾው፣ ወዘተርፈ ላይ የፈጸመው የዘር ፍጅት፣ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ሊፈጸም ቀርቶ ለማሰብ አስቸጋሪ ነው። ግፉ ከገደቡ አልፎ በመትረፍረፉ፣ የዚህ የከፋ የዘር ፍጅት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ሰለባ የሆኑት ነገዶች...Read more

በቴሌኮንፈረንስ ለሚደረግ ስበስባ ጥሪ! በዓለም ዙሪያ ለምትኖሩ የሞረ ሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት አባሎች፤ ደጋፊዎች እና አገር ውዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ

Wednesday, August 24, 2016

የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ አባሎቹና ደጋፊዎቹ እንዲሁም ሞረሽ የዐማራ ሬድዮ ድምፅ ፕሮጀክትን የሚደግፉ ኢትዮጵያን ክሆኑ ወገኖቻችን ጋር በቴሌኮንፈረንስ(በሥልክ) ስብሰባ ለማድረግ አቅዷል። ስብሰባው ቅዳሜ  ቀን  ነሓሴ ፳፩ ፤፪ሺህ ፰ዓ.ም(August 27፣2016) በኒዮርክ ሰዓት አቆጣጠር በ3:00PM ይጀመራል። የስብሰባው ዓላማ ሞረሽ የዐማራ ሬድዮ ድምፅ ፕሮጀክትን እውን ለማደረግ የሚያስችል የገንዘብ እና ሌሎች ዓይነት ድጋፎችን ለማሰባሰብ...Read more

በባሕርዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ በትግሬ-ወያኔ ግፍ የተጨፈጨፉትን እንድናውቃቸውና እንድንዘክራቸው!

Thursday, August 18, 2016

ዘረኛው የትግሬ ወያኔ የወልቃይት ጠገዴን የማንነት ጥያቄ ደግፈው በወጡ የባሕርዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ በግፍ የገደላቸው ወገኖቻችን ዝርዝር በከፊል።

«የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ፣ የእኛም የዐማራነት ጥያቄ ነው፣» ብለው እሑድ ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓም ላይ በባሕርዳር ከተማ፣ በሰላማዊ መንገድ ድምፃቸውን ለማሰማት በወጡ ዐማሮች ላይ፣ የትግሬ ወያኔ ዘረኛ ቡድን በርካታ፣ ሩቅ አሳቢ፣ ለሥራ የጓጉ፣ ላገርና ለወገን ታላቅ ተስፋ...Read more

የሕዝቡ እንቢተኝነት ፣ የዘረኛውን የወያኔ አገዛዝ እያፈራረሰው ነው!

Wednesday, August 17, 2016

የትግሬ ወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ላይ ላለፉት 25 ዓመታት ጭኖት የኖረው በዘረኝነት ላይ የተመሠረተው ያንድ ነገድ የበላይነትና የውስጥ ቅኝ አገዛዝ ሥርዓት በሕዝቡ የእንቢተኝነት እንቅስቃሴ ከመኖር ወደ አለመኖር እየተሸጋገረ ነው። የወያኔ አገዛዝ ሲጀመር ጀምሮ ደካማ «መንግሥት» እንደሆነ ይታወቃል። የድክመቱ መገለጫም፣ አንደኛ፣ የአናሳዎች መንግሥት በመሆኑ የአብዛኛውን ሕዝብ ድጋፍ ያገኘ አይደለም። ሁለተኛ፣ የሚገዛው በኃይል በጦር መሣሪያ አስገድዶ እንጂ፣ በሕግ...Read more

የትግሬ-ወያኔ የዐማራ እና የኦሮሞ ነገዶችን ሕዝብ ጨርሶ ለማጥፋት ያቀደው ሚስጢራዊ አዲስ ሤራ

Tuesday, August 16, 2016

ላለፉት 25 ዓመታት የትግሬ-ወያኔ በሕዝብ ላይ የፈጸመው ግፍና በደል ከመጠን በላይ በመሆኑ፣ ሕዝቡን ለእምቢተኝነት አነሳስቷል። ይህ ግፍና በደል መጠን የለሽ በመሆኑ፣ በአገሪቱ ልዩ ልዩ ክፍሎች፣ በተለይም በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋ፣ በወሎ፣ በሐረርጌ፣ በአርሲና በወለጋ ክፍለ-ሀገሮች የሚኖረው ሕዝብ፣ የትግሬ-ወያኔ «ለብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ዕኩልነት» ሲል «አመጣሁት» ያለውን «ሕገ-መንግሥት» የማይቀበለው መሆኑንና፣ የዚሁ  «ሕገ-መንግሥት» ተብየ መገለጫ...Read more

ቅኝ ተገዥነቱን ያወቀ ሕዝብ በከፊል ነፃ ነው!

Saturday, August 13, 2016

ኢትዮጵያ ሕዝብ በትግሬ ወያኔ ቅኝ ተገዥ ከሆነ ድፍን 25 ዓመት ሆነው። በእነዚህ ረጅም ዓመታት፣ የተማሩትም ሆነ ያልተማሩት ዜጎች፣ በቅኝ ተገዥነት መያዛቸውን ያወቁትም ሆነ ለማወቅ የጣሩት በጣም ጥቂቶች ናቸው። እነዚህ በቅኝ ተገዥነት ተይዘናል ያሉት የጥቂቶቹ ድምፅ፣ በብዙኃኑ፣ ከሁሉም በላይ በጎሣ ፖለቲከኞቹ ድምፅ ተውጦ፣ ወያኔ፣ ያላንዳች ሀግ ባይ፣ ሩብ ምዕተ ዓመታት  የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅምና ሉዓላዊነት በእጅጉ የጎዱ ሥራዎችን እንዲሠራ ሠፊ ዕድል ሰጠው።...Read more

Pages

Subscribe to RSS - Amharic