MWAO Press Releases

Thursday, April 28, 2016

ሀ)   መግቢያ

ኢትዮጵያ ውስጥ በአንድነት ሃይሎችና በጎጠኞች መካከል የተካሄደው ፍልሚያ ፤ በጎጠኞች አሸናፊነት ከተደመደመ ወዲህ እራሱን የቻለ የፖለቲካ ውጥንቅጥ እስከትሎ እንደሚመጣ የተገመተ ቢሆንም ወደ ዘር ማጥፋትና ማጽዳት ያመራል ብሎ የተነበየ ከቶ አልነበረም። የጎጠኞች ያልተጠበቀ ድልና እሱንም ተከትሎ የመጣው ስካር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዐማሮችን ደም አፍሷል፤ እያፈሰሰም ነው። ክረምትና በጋ ፣ ቁር ፣ ሃሩር ሳይለይ ሌት ተቀን ሳይባል፤ ምስራቅ ይሁን ሰሜን ሳይል ፣ ክብረ በአልና የሰርክ ቀናት ሳይለይ ፣ ከ1983 እስከ ያዝነው 2008 ዓ.ም  የዐማሮች እጣ ፋንታቸው መፈናቀልና መገደል ሆኗል። እንደከብት የታረዱት ፣ እሳት የበላቸው ፣ በግፍ ያለቁት በሺዎችና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት ዐማሮች ደም በኢትዮጵያ ምድር በአራቱም ማእዘናት በመጮህ ላይ ነው!

Friday, April 8, 2016

የማንኛውም አመፅ መነሻ መሠረቱ፣ ገዥዎች በሕዝብ ላይ የሚያደርሱት፣ የኢኮኖሚ ብዝበዛ፣ የመብት ረገጣ፣ የማንነት ነጠቃ እና የሥነ-ልቦና ሰለባ ልኩን አልፎ ገደብ ሲጥስ የሚፈጥረው ምሬት እንደሆነ ይታወቃል። የትግሬ ወያኔ ዘረኛ እና ከፋፋይ የፋሽስት ሞሶሎኒ ዓላማ አራማጅ ቡድን፣ በወልቃት ፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በሠቲት እና በአርማጭሆ ሕዝብ ላይ በተናጠል፣ እንዲሁም  በዐማራው ነገድ ላይ በወል፣ ከፍተኛ የሆነ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ከ1972 ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት 36 ዓመታት በተከታታይ ፈጽሟል፤ እየፈጸመም ነው። በዚህ ረገድ የወረዳ ግዛቶቹም ሆኑ ነዋሪው ሕዝብ በየትኛውም ጊዜ፣ የትግራይ የግዛት አካል ሆነው አያውቁም። የትግሬ ግዛት ደንበርም ተከዜን ተሻግሮ አያውቅም። ሕዝቡም ጥንትም ሆነ ዛሬ፣ በጉርብትና ከሚናገረው ትግርኛ፣ ዐረብኛ እና መሰል ቋንቋዎች በቀር፣ የትግሬነት ባህል፣ ታሪክ፣ ወግ፤ ሥነልቦና እና መሰል የማንነት ማረጋገጫ ዕሴቶች ኖሮት አያውቅም፤ እንዲኖረውም አይሻም። 

Wednesday, April 6, 2016

Moresh Wogenie Amara Organization (MWAO), which sponsored the study on the Crime of Ethnic Cleansing Perpetrated on the Amhara of Ethiopia, 1991-2016, is an Amhara Organization based in America. It is legally registered in Maryland, USA, as a civic society and has branches all over the world. The Amhara is one of the two major ethnic groups in Ethiopia. MWAO aspires to share the plight of the Amhara with nations who stand for justice in general and with concerned human rights organizations in particular. 

Tuesday, March 29, 2016

ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ ለኢትዮጵያ ክብር፣ ነፃነት፣ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ማንነት ሲሉ፣ እጃቸውን ለእንግሊዝ ጦር መሪ ጄኔራል ናፒየር ከሚሰጡ ሞትን በመምረጥ ሽጉጣቸውን ጠጥተው ለኢትዮጵያዊነት ዳብሮ መቀጠል የተሰው ሰማዕት ንጉሠ ነገሥት መሆናቸው ዓለም ያወቀውና ያደነቀው አንጸባራቂ የታሪካችን አንዱ አካል ነው። ቴዎድሮስ ከእርሳቸው የነበሩት ንጉሦች መሠረታቸውን ይፋት፣ ሐረርና አዳል ባደረጉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ጋር ባደረጉት ተከታታይ ጦርነቶች፣ ተያይዞም ከግራኝ ጋር በተካሄደው እጅግ አውዳሚ አሥራ አምስት ዓመታት ያስቆጠረ ጦርነት፣ በኋላም የግራኝን እግር በመከተል በተከሰተው የጋላ (ኦሮሞ) ወረራ የሕዝቡ አንድነት ላላቶ፣ የኢኮኖሚ አቅሙ መድቀቅ የተነሳ በተፈጠረው ሁለንተናዊ ድክመት የተከሰተውን የዘመነ መሣፍት አገዛዝ ዘመን የተፈጠሩ የዚያን ወቅት ኅብረተሰብ ልጅ ናቸው። ቴዎድሮስ አገሪቱ በየአካባቢው የጦር አበጋዞች ተሸንሽና፣ የዘውዱ የአንድነት ምልክትነቱና የሥልጣን ምንጭነቱ ጥያቄ ውስጥ ወድቆ ከ70 ዓመታት ላላነሰ በዘለቀው «ዘመነፍዳ» የብላ ተባላ ዘመን፣ በቆራጥነት ታግለው፣ የአገሪቱን አንድነት ትናሣዔ ያበሰሩ ጀግና መሪ መሆናቸው ማንም ሊጠራጠረው ያልቻለ ሥብዕና ባለቤት ናቸው። ለዘመናዊ ኢትዮጵያ አስተዳደር ጽኑ መሠረት የጣሉ፣ ከሁሉም በላይ የዘውዱንና የንጉሠ ነገሥቱን መብትና ሥልጣ መልሶ ተገቢ ቦታውን እንዲይዝ ያደረጉ ራዕየ ሠፊ፤ ብልኅ፣ አስተዋይ፣ ቆራጥና ጀግና ንጉሠ ነገሥት መሆናቸው ይታወቃል። 

Monday, November 18, 2013

የዘመናዊ  ትምህርት  ወይም  “ቀለም  ቀመስ”  የሆነው  የዐማራው  ትውልድ  በሌሎች  ነገዶች/ጎሣዎች  ቀለም  ቀመስ ትውልድ  ተክዷል።  በሌሎች  መካዱን  ያልተረዳውና  ሊረዳም  ያልፈለገው  ቀለም  ቀመሱ  የዐማራ  ትውልድ፣  የራሱን  ማንነት ክዶ  የገዛ  ትውልዱን  ከጥፋት  ለመከላከል  የሚያስችለውን  አቅሙን  ላለመጠቀም  የተለያዩ  ምክንያቶችን  በመደርደር  ራሱንና ወገኖቹን ለጥፋት አጋልጦ፣ “የራሷ ሲያርባት የሰው ታማስላለች” ዓይነት ሆኖ ይታያል። ልብ እንበል ፣ ልብ በሉ!

Pages